የፌደራል የስነምግባርና የፀረሙስና ኮሚሽን
ቅጹ ከመሞላቱ በፊት በጥንቃቄ የሚነበብ ማሳሰቢያ!
-
ሆን ብሎ ትክከል ያልሆነ ወይም ሐሰተኛ መረጃ መስጠት አግባብ ባለው የወንጀል ህግ ድንጋጌ መሰረት ስከሚያስቀጣ እውነትኛ እና ትክክለኛ መረጃ ብቻ ይስጡ!
-
የሚሞሉት የሀብት መረጃ ዓይነት ከሌለዎት ወደ ሚቀጥለው ገጽ መሄድ ይችላሉ።
-
የሚመዝገበው ሀብት ና ገቢ የእርስዎ እና የትዳር ጓደኛዎ የጋራ ሀብት፣ የእርስዎ የግል ሀብት፣ የእርስዎ የትዳር ጓደኛ የግል ሀብት፣ እድሜያቸው ከ 18 ዓመት ብታች የሆኑ ልጆችዎን እና በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር የሚገኝ ሀብትን ሁሉ ያካትታል።
-
በውርስ ተገኝቶ ያልተከፋፈለ ሀብት፣ በቅንጦት ዕቃነት የማይፈረጅ የቤት ቁሳቁስ እና ከጡረታ የሚገኝ ገቢ አይመዘገብም።
-
ማናቸውም መሳሪያ እና የአየርና የባህር ትራንስፖርት መገልገያ አዲስ የሚባለው አንድ አመት እና ከአንድ አመት በታች ያገለገለ ሲሆን ነው።
-
ማንኛውም ዓይነት ቤት/ባዶ ቦታ ካሎት መረጃውን በአግባቡ ይሙሉ።
-
ማንኛውም ዓይነት የንግድ ድርጅት ካሎት መረጃውን በአግባቡ ይሙሉ።
-
ማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ ከሞተር ሳይክል ጀምሮ ካሎት መረጃውን በአግባቡ ይሙሉ።
-
ማንኛውም ዓይነት የባንክ ደብተር ቁጥር እና የገንዘብ መጠን መረጃውን በአግባቡ ይሙሉ።
-
ማንኛውም ዓይነት በብድር እና ቁጠባ ማህበራት ተቀማጭ የገንዘብ መጠን መረጃውን በአግባቡ ይሙሉ።
-
ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ጌጣጌጥና የከበረ ማዕድን ሀብት ወርቅ ከሆነ 50 ግራም እና በላይ እንዲሁም አልማዝ፣ዕንቁ እና ሌሎች በማንኛውም ግራም ደረጃ ይመዘገባሉ።
-
ልዩ ልዩ ገብዎች ከትርፍ ስዓት፣ከኪራይ፣ ከዕድል ሎተሪ፣ ከውጪ ጉዞ ወዘተ... የተገኘ ገቢን ያካትታል።
-
በወንድ ጾታ የተገለጸው ሁሉ የሴትንም ጾታ ይመለከታል።